ጥራት ያለው ት/ት ለሀገር እድገት ለሰው ልጆች ስብእና እንዲሁም ክብር ወሳኝ ነው። ት/ት ቤቶች ደግሞ ለዚህ መሳከት ትልቅ ሚና አላቸው።
በዚህ ረገድ በሀጋራችን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ብኖሩም በተግባር ሲታይ እያጋጠመ ያለው ችግር እጅግ ከፍተኛ መሆኑ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት አንድ ማሳያ ነው።

ይህን ችግር ለመቅረፍ ና በ2016 የተሻለ ውጤት ለማምጣት አርሲ ዩኒቨርሲቲ አንድ መርሃግብር በማውጣት በዛሬው ቀን ከአሰላ ከተማ ና አርሲ ዞን ወረዳ ት/ት ቤቶች ለመጡ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል በማሳወቅ ውይይት አድርጓል። ለመርሃግብሩ ስኬት የዩኒቨርስቲ መምህራን ና አስተዳዳር ት/ት ቤቶችን ለማብቃት ድጋፍ እንድሚያደርጉና በ2016 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ፕሬዚዳንት
ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ ገልጸዋል። በተጨማሪም የአርሲ ዩንቨርሲቲ ሞዴል ት/ት ቤት የ2016 ተፈታኞችን 100% ለማሳለፍ እየተሰራ ሲሆን ተማሪዎችንም ለማበረታታት ከክፍላቸው ከፍተኛው ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች 5 ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ፕሬዚዳንቱ በሽልማት አበርክቶላቸዋል።

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በአርሲ ዞን የሚገኙ በ2016 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ  ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን ለማብቃት ሥራ ጀመረ።

አርሲ ዩኒቨርሲቲ  የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች ዉጤት እንደ ሀገር አደጋ  ዉስጥ የገባዉን ለመታደግ በአርሲ ዞን የሚገኙ  የሁለተኛ ደረጀ ት/ቤቶች የብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን 50% እና በዩኒቨርሲቲዉ ሥር የሚተዳደረዉ  አሰላ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት  ተማሪዎችን ደግሞ 100% የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት እንድያስመዘግቡ  ተግተዉ እንደሚሠሩ አሳዉቋል።
ዩኒቨርሲቲዉ በዞኑ የሚገኙትን የትምህርት ባለሙያዎዎችን፣ መምህራን፣ የተማሪዎች ቤተሰቦችን፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን፣  ርዕሠ መምህራንና ባለድርሻ አካላትን ፣ የሀይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች እንደ ሀገር የገጠመንን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዉጤት ቀዉስ ላይ ለመወያየት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ  የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተገኙበት ወቅት ነዉ ዩኒቨርሲቲዉ ቁርጠኝነቱን የገለፀዉ።
ዉይይቱን የመሩት የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ እና የኦሮሚያ ት/ቢሮ ም ኃላፊ  ዶ/ር ገላና ወ/ሚካኤል ስሆኑ፤ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶር ዱጉማ  አዱኛ እቅዱን የሚያሳኩበትን ስትራቴጂ ለተሰብሳቢዎቹ እንዲህ በማለት አብራርቷል፡
” አርሲ ዩኒቨርሲቲ  እንደ ሀገር የድርሻዉን ለመወጣት ከዚህ ቀደም ለአካባቢ ህብረተሰብ ስሰጥ የነበረዉን የማህበረሰብ አገልግሎት በዘንድሮ አመት  ደግሞ ያለንን አቅም በማደራጀት ሙሉ በሙሉ በዞኑ የሚገኙትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ  ፈተና ተፈታኞችን በማገዝ 50% ፈተናዉን እንድያልፉ ማድረግ፤ የአሰላ ልዩ  2ኛ ትቤት ደግሞ 100% ማሳለፍ ይሆናል። ሁለት  መሠረታዊ ስትራቴጂዎች በመጠቀም ተማሪዎቻችንን እናበቃለን።

  • በመረዳዳት/በመተባባር የመማር (Collaborative Learning)
  • ትምህርት ቤቶችን በማገናኘት በማስተሳሰር (Connected Schools) ስትራቴጅዎችን ከግብ ለማድረስ የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና መምህራን ፣ ተማሪዎችና የተማሪዎች ቤተሰቦች  ከፍተኛ ኃላፊነት አላባችሁ።
    በመሆኑም  ከዚህ  ከዉጤት  ቀዉስ ለመዉጣት የአርሲ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና  ማናጅመንቱ በቁጭት  ለመሥራት መወሰናችንን አሳዉቃለሁ”። ብሏል።
    በመጨረሻም የአርሲ ዩኒቨርሲቲ አሳላ ልዩ  2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ1-3 ደረጃ ያላቸዉን የማበረታቻ ሽልማት በመሸለም ፡ ዉይይቱ ተጠናቋል።

IMAGINE the Possibilities!

Barnoonni qulqullina qabu guddina biyyaa fi kabaja dhala namaatiif barbaachisaa dha. Kana galmaan ga’uuf manneen barnootaa gahee olaanaa qabu. Bu’aan qormaata ba’uu kutaa 12ffaa bara 2015 akka agarsiisutti gama kanaan biyya keenya keessatti hojiiwwan hojjetamaa jiran jiraatanis rakkoon qabatamaan mudachaa jiru baayyee ol’aanaadha. Rakkoo kana hiikuuf bara 2016 bu’aa fooyya’aa galmeessisuuf Yuunivarsiitiin Arsii sagantaa baasee barattoota kutaa 12ffaa, barsiisota, Maatii fi kutaalee hawaasaa adda addaa manneen barnootaa Magaalaa Asallaa fi Aanota Zoonii Arsii irraa dhufan waliin har’a marii gaggeessee jira. Milkaa’ina sagantichaatiif barsiisonni fi bulchitoonni Yuunivarsiitii manneen barnootaa deeggaruun bara 2016 bu’aa fooyya’aa galmeessisuuf hojjechuu qabu akka qaban Dr. Dugumaa Adugnaa ibsaniiru. Kana malees, Manni Barumsaa Moodeela Yuunivarsiitii Arsii qormaata bara 2016 %100 dabarsuuf hojjechaa kan jiru yoo ta’u, barattoota jajjabeessuuf Pirezidaantiin Yuunivarsiitii Arsii barattoota kutaa isaanii keessatti bu’aa olaanaa galmeessisaniif kompiitara laptop ammayyaa 5 badhaasaniiru.

Ni dandeenya, akkuma Atleetota Keenyaa!

Leave a Comment