የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
ሚያዝያ 03/ 2017 ዓ.ም
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ በዩኒቨርቲው በመገኘት ከዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም የስድስት ወር እቅድ አፈፃጸም ሪፖርት በእስትራቴጅክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡
የውይይት መድረኩን የመሩት ዶ/ር ሶፊያ ካሳ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በቀረበው ሪፖርት ላይ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ነጥቦች በማንሳት ሀሳብ እንድሰጥበት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር ሶፊያ እና የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የቀረበውን ሪፖርት በማድነቅ በዚሁ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል፡፡







የሥራ አመራር ቦርዱ ዩኒቨርሲቲው የጀመረውን የሪፎርም ስራ አጠናክሮና ቅድሚያ መሰጠት የሚገባቸውን ጉዳዮች ለይቶ መስራቱን መቀጠል እንዳለበት በመግለፅ ቦርዱም አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ እንዳለበት አፅእኖት ሰጥቷል፡፡ በተለይ የዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጀክቶች ከዚህ በፊት መጓተት ይታይባቸው ስለነበረ አሁን በዩኒቨርሲቲው አመራር እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች እጅግ የሚበረታቱ መሆኑን በመግለፅ የክትትልና ቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ መሄድ እንዳለበት በማሳሰብ የቀረበውን ሪፖርት አፅድቋል፡፡
በሌላ በኩል የሥራ አመራር ቦርዱ በተለያዩ ከምፓሶች በመገኘት የዩኒቨርሲቲውን የግንባታ ፕሮጀክቶችን በአካል ጎብኝቷል፡፡ በአካል ምልከታው ወቅት ከፕሮጀክቱ ኮንተራክተሮች ጋር በመገናኘት አንድ አንድ በተመለከቷቸው ክፍተቶች ላይ ምክረ ሀሳባቸውን ለግሰዋል፡፡ በማጠቀለያም በቀረበው ሪፖርት እና በግንባታ
ፕሮጀክቶቹ የታዩ እምርታዎችን በማድነቅ የወደፊት አቅጣጫ እና የሥራ መመሪያን በመስጠት ውይይቱ ተቋጭቷል፡፡
እንደ ክዋክብት አትሌቶቻችን፤ የላቁ ባላሙያዎች!